የተርቲል አርማተርቲልቀጥታ ሬዲዮ

ሱራ አት ቲን፦ ጽሑፉ እና የቁርኣን ፍቺ ትርጉሙ

በሙስሐፉ ውስጥ 95ኛው ሱራ ነው፤ 8 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 597 ይጀምራል።

ቲላዋዎቹን አዳምጥይህን ሱራ በሙስሐፉ ከተፍሲር ጋር አንብብ‹ ሱራ አሽ ሸርህሱራ አል ዐለቅ ›

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

1. በበለስና፤ በወይራ ዛፍ እምላለሁ፣

2. በሲና ተራራም፤

3. በዚህ በጸጥተኛው (ጸጥታ በነገሰበት) አገር (መካም) እምላለሁ።

4. በርግጥ ሰውን በጣም በአማረ አቋም ላይ ፈጠርነው።

5. ከዚያም (ከፊሉን) ከበታቾች ሁሉ በታች አድርገን መለስነው።

6. እነዚያ በአላህ ያመኑትና መልካም ተግባራት የሰሩት ሲቀሩ ለእነርሱማ የማይቋረጥ ምንዳ አለላቸው።

7. (የሰው ልጅ ሆይ) ታዲያ ከዚህ (እውነታ) በኋላ በፍርዱ ምን አስተባባይ አደረገህ?

8. አላህ ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ፈራጅ አይደለምን?

የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)

ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።

ቲላዋዎቹን አዳምጥይህን ሱራ በሙስሐፉ ከተፍሲር ጋር አንብብ‹ ሱራ አሽ ሸርህሱራ አል ዐለቅ ›