በሙስሐፉ ውስጥ 106ኛው ሱራ ነው፤ 4 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 602 ይጀምራል።
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
1. ቁረይሽን ለማላመድ (ባለ ዝሆኖቹን አጠፋ)።
2. የክረምትንና የበጋን ወራት ጉዞዎች ሊያላምዳቸው ይህንን ሰራ፤
3. ስለዚህም የዚህን ቤት (የካዕባን) ጌታ ብቻ ያምልኩ።
4. ያንን ከርኃብ ያበላቸውን፤ ከፍርሃትም ያዳናቸውን (ጌታ ብቻ ያምልኩ)።
የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)
ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።