የተርቲል አርማተርቲልቀጥታ ሬዲዮ

ሱራ አል ማዑን፦ ጽሑፉ እና የቁርኣን ፍቺ ትርጉሙ

በሙስሐፉ ውስጥ 107ኛው ሱራ ነው፤ 7 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 602 ይጀምራል።

ቲላዋዎቹን አዳምጥይህን ሱራ በሙስሐፉ ከተፍሲር ጋር አንብብ‹ ሱራ ቁረይሽሱራ አል ከውሰር ›

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንን በፍርዱ ቀን የሚያስተባብለውን ሰው አየህን? (አወከውን?)

2. ይሀውም ያ የቲምን በኃይል የሚገፈትረው፤

3. ድሃን በማብላት ላይም የማያነሳሳው ነው።

4. ወዮላቸው ለሰጋጆች፤

5. ለእነዚያ እነርሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለሆኑት (ሰጋጆች)፤

6. ለእነዚያ እነርሱ ይዩልኝ ባዮች ለሆኑት፤

7. የዕቃ ትውስትንም ሰዎችን የሚከለክሉ ለሆኑት ሁሉ ወዮላቸው።

የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)

ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።

ቲላዋዎቹን አዳምጥይህን ሱራ በሙስሐፉ ከተፍሲር ጋር አንብብ‹ ሱራ ቁረይሽሱራ አል ከውሰር ›