የተርቲል አርማተርቲልቀጥታ ሬዲዮ

ሱራ አል ፊል፦ ጽሑፉ እና የቁርኣን ፍቺ ትርጉሙ

በሙስሐፉ ውስጥ 105ኛው ሱራ ነው፤ 5 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 601 ይጀምራል።

ቲላዋዎቹን አዳምጥይህን ሱራ በሙስሐፉ ከተፍሲር ጋር አንብብ‹ ሱራ አል ሁመዛህሱራ ቁረይሽ ›

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ አላህ በዝሆኑ ባለቤቶች ላይ እንዴት እንደሰራ አላወቅክምን?

2. ተንኮላቸውን በጥፋት ውስጥ ከንቱ አላደረገምን?

3. በእነርሱ ላይ መንጎች የሆኑን ወፎችንም ላከ።

4. ከተጠበሰ ጭቃ የሆነን ጠጠር የምትወረውርባቸውን (አእዋፍ)

5. እና ቅጠሉ እንደ ተበላ አዝመራ አደረጋቸው

የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)

ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።

ቲላዋዎቹን አዳምጥይህን ሱራ በሙስሐፉ ከተፍሲር ጋር አንብብ‹ ሱራ አል ሁመዛህሱራ ቁረይሽ ›