በሙስሐፉ ውስጥ 99ኛው ሱራ ነው፤ 8 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 599 ይጀምራል።
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ምድር በኃይል መንቀጥቀጧን በተንቀጠቀጠች ጊዜ፤
2. ምድርም ሸክሞቿን ባወጣች ጊዜ፤
3. ሰዉም "ምን ሆነች?" ባለ ጊዜ፤
4. በዚያ ቀን ወሬዎቿን ትናገራለች።
5. ጌታህ ለእርሷ አሳውቋታልና፤
6. በዚያ ቀን ሰዎች ሁሉ ስራዎቻቸውን እንዲያዩ ይደረጉ ዘንድ (እንደየስራቸው) የተበታተኑ ሆነው (ከየመቃብራቸው ወደ መቆሚያው ስፍራ) ይመለሳሉ።
7. የብናኝን ክብደት ያህል መልካም የሰራ ሰው ያገኘዋል።
8. የብናኝን ክብደት ያህል ክፋት የሰራ ሰውም ያገኘዋል።
የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)
ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።