በሙስሐፉ ውስጥ 1ኛው ሱራ ነው፤ 7 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 1 ይጀምራል።
1. በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።
2. ምስጋና ሁሉ ለዓለማቱ ጌታ፣ ለአሏህ ይገባው።
3. እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ ለሆነው።
4. የፍርዱ ቀን ባለቤት ለሆነው (ለአላህ ብቻ ይገባው)።
5. (ሙስሊሞች ሆይ! ጌታችሁን) አንተን ብቻ እንገዛለን። ካንተም ብቻ እርዳታን እንለምናለን (በሉት)።
6. ቀጥተኛውን መንገድ ምራን።
7. የእነዚያን ለእነርሱ በጎ የዋልክላቸውን፤ በእነርሱ ላይ ያልተቆጣባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን በሉ)።
የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)
ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።