በሙስሐፉ ውስጥ 88ኛው ሱራ ነው፤ 26 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 592 ይጀምራል።
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሸፋኝቱ ትንሳኤ ወሬ መጣልህን?
2. በዚያ ቀን (የከሓዲያን) ፊቶች ተዋራጆች ናቸው።
3. ሰሪዎች ለፊዎች ናቸው።
4. የምታቃጥልን እሳት ይገባሉ።
5. በጣም ከፈላች ምንጭም ይጋታሉ።
6. ዶሪዕ ከሚባል (እሾሃማ) ዛፍ እንጂ ሌላ ምግብ የላቸዉም።
7. አካልን አያሰባ፤ ከረኃብም አያብቃቃ፤
8. (የአማንያን) ፊቶች በዚያ ቀን ተቀማጣዮች ናቸው።
9. በስራቸውም ተደሳቾች ናቸው።
10. በከፍተኛ ገነት ውስጥ ናቸው።
11. በውስጧ ውድቅን ነገር አይሰሙም።
12. በውስጧ ፈሳሾች ምንጮች አሉ።
13. በውስጧ ከፍ የተደረጉ አልጋዎች አሉ።
14. በተርታ የተኖሩ ኩባያዎችም፤
15. የተደረደሩ መከዳዎችም፤
16. የተነጠፉ ስጋጃዎችም (አሉ)።
17. (ከሓዲያን) ግመል እንዴት እንደተፈጠረች አይመለከቱምን?
18. ሰማይም እንዴት ከፍ እንደተደረገች!
19. ተራራዎችም እንዴት እንደ ተቸከሉ!
20. ምድርም እንዴት እንደተዘረጋች አይመለከቱምን?!
21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አስታውስም። አንተ አስታዋሽ ብቻ ነህና።
22. በእነርሱ ላይ አስገዳጅ (ተሿሚ) አይደለህም፤
23. ግን ከእውነት የዞረና የካደ፤
24. አላህም ከባዱን ቅጣት ይቀጣዋል።
25. መመለሻቸው ወደ እኛ ብቻ ነው።
26. ከዚያም ምርመራቸው በእርግጥ በእኛ ላይ ብቻ ነው።
የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)
ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።