በሙስሐፉ ውስጥ 114ኛው ሱራ ነው፤ 6 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 604 ይጀምራል።
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ) በል፡ -በሰዎች ጌታ እጠበቃለሁ፤
2. የሰዎች ሁሉ ንጉስ በሆነው ጌታ፤
3. የሰዎች ሁሉ አምላክ በሆነው ጌታ፤
4. ከዚያ ብቅ እልም ባይ ከሆነው ጎትጓች ክፋት፤
5. ከዚያ በሰዎች ልቦች ውስጥ የሚጎተጉት (ከሆነው፤)
6. ከጂንም ይሁን ከሰው (ሰይጣን) ክፋት (እጠበቃለሁ)።
የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)
ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።