በሙስሐፉ ውስጥ 90ኛው ሱራ ነው፤ 20 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 594 ይጀምራል።
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
1. በዚህ ሀገር (በመካ) እምላለሁ
2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ በዚህ አገር (መዋጋት) የተፈቀደልህ ስትሆን።
3. በወላጂና በወለዳቸውም (በአደምና በዘሮቹ) ሁሉ (እምላለሁ)።
4. ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ሆኖ ፈጠርነው።
5. በእርሱ ላይ አንድም አካል የማይችል መሆኑን ያስባልን?
6. "ብዙን ገንዘብ አጠፋሁ" ይላል፤
7. አንድም ያላየው መሆኑን ያስባልን?
8. ለእርሱ ሁለት አይኖችን አላደረግንለትንምን?
9. አንድ ምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፤
10. ሁለትን መንገዶችስ አልመራነዉምን?
11. ዐቀበቱን አልወጣም።
12. ዐቀበቱን መውጣት ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?
13. ያ ጫንቃን መልቀቅ ነው። [1]
[1] ባሪያን ነጻ ማውጣት ማለት ነው
14. ወይም የረሀብ ባለቤት በሆነ ቀን (ረሀብተኛን) ማብላት፤
15. የዝምድና ባለቤት የሆነን የቲም፤
16. ወይም የአፈር ባለቤት የሆነን (ችግረኛ) ማብላት ነው።
17. ከዚያም ከእነዚያ በአላህ ካመኑትና በመታገስና በመተዛዘንም ላይ አደራ ከተባባሉት ሰዎች ጋር መሆን ነው።
18. እነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው።
19. እነዚያ በአናቅጻችን የካዱ ሁሉ እነርሱ የግራ ጓዶች ናቸው።
20. ለእነርሱ የምትዘጋባቸው እሳትም አለች።
የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)
ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።