የተርቲል አርማተርቲልቀጥታ ሬዲዮ

ሱራ አል ቡሩጅ፦ ጽሑፉ እና የቁርኣን ፍቺ ትርጉሙ

በሙስሐፉ ውስጥ 85ኛው ሱራ ነው፤ 22 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 590 ይጀምራል።

ቲላዋዎቹን አዳምጥይህን ሱራ በሙስሐፉ ከተፍሲር ጋር አንብብ‹ ሱራ አል ኢንሺቃቅሱራ አጥ ጣሪቅ ›

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

1. የህብረ ከዋክብት ባለቤት በሆነችው ሰማይ፤

2. በተቀጠረዉም ቀን፤

3. በመስካሪና በሚመሰከርበትም እምላለሁ።

4. የጉድቡ ባለቤቶች ተረገሙ።

5. የባለማገዶዋ እሳት ባለቤቶች።

6. እነርሱ በርሷ (አፋፍ) ላይ ተቀማጮች በሆኑ ጊዜ (ተረገሙ)።

7. እነርሱም በምዕመኖች ላይ ለሚሰሩት (ማሰቃየት) መስካሪዎች ናቸው።

8. ከእነርሱም በአሸናፊውና በምስጉኑ አላህ ማመናቸውን እንጂ ሌላን ምንንም አልጠሉም።

9. ያ የሰማያትና የምድር ንግስና ለእርሱ ብቻ የሆነውን (ነው ያመኑበት)። አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነው (አዋቂ ነው)።

10. እነዚያ አማኞችና ምዕመናትን ያሰቃዩና ከዚያ ያልተጸጸቱ ሁሉ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አለላቸው። ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አላቸው።

11. እነዚያ በአላህ አምነው መልካም ስራዎችን የሰሩ ሁሉ ለእነርሱ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች አሏቸው። ይህ ታላቅ ስኬት ነው።

12. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህ በኃይል መያዝ ብርቱ ነው።

13. እነሆ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፤ ይመልሳልም።

14. እርሱም ምህረቱ የበዛ ወዳድ ነው።

15. የላቀው የዙፋኑ ባለቤት ነው።

16. የሚሻውን ሁሉ ሰሪ (ፈፃሚ) ነው።

17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! የእነዚያ ነብያትን ያስተባበሉ) ሰራዊቶች ወሬ መጣልህን?

18. የፊርዓውንና የሰሙድ (ወሬ ደርሶሃልን)?

19. ይልቁንም እነዚያ (በአላህ) የካዱት (ሰዎች ሁሉ) እውነትን በማስተባበል ውስጥ ናቸው።

20. አላህም በዙሪያቸው (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው።

21. ይልቁንም እርሱ የተከበረ ቁርኣን ነው።

22. የተጠበቀ በሆነ ሰሌዳ (ሎህ) ውስጥ ነው።

የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)

ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።

ቲላዋዎቹን አዳምጥይህን ሱራ በሙስሐፉ ከተፍሲር ጋር አንብብ‹ ሱራ አል ኢንሺቃቅሱራ አጥ ጣሪቅ ›