የተርቲል አርማተርቲልቀጥታ ሬዲዮ

ሱራ አል ለይል፦ ጽሑፉ እና የቁርኣን ፍቺ ትርጉሙ

በሙስሐፉ ውስጥ 92ኛው ሱራ ነው፤ 21 አንቀጾች አሉት፤ በገጽ 595 ይጀምራል።

ቲላዋዎቹን አዳምጥይህን ሱራ በሙስሐፉ ከተፍሲር ጋር አንብብ‹ ሱራ አሽ ሸምስሱራ አድ ዱሓ ›

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

1. በሌሊቱ (በጨለማው) በሚሸፍነው ጊዜ፤ (እምላለሁ)።

2. በቀኑም በተገለጸ ጊዜ፤

3. ወንድንና ሴትን በፈጠረዉም (አምላክ) እምላለሁ።

4. ስራችሁ በእርግጥ የተለያየ ነው።

5. ያ! የሰጠና ጌታውንም የፈራማ፤

6. በመልካሚቱ (እምነትም) ያረጋገጠ ሰው

7. ለገሪቱ እናገራዋለን።

8. ያ! የሰሰተ በራሱም የተብቃቃ፤

9. በመልካሚቱም ያስተባበለውማ

10. ለክፋት እናዘጋጀዋለን።

11. (ወደ ገሀነም) በወደቀ ጊዜ ያ! ገንዘቡ ከእርሱ ምንም አይጠቅመዉም።

12. ቅኑን መንገድ መግለጽ በእኛ ላይ አለብን።

13. መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም ዓለም የእኛው ነው።

14. የምትንቀለቀል እሳት አስጠነቀቅኳችሁ።

15. ከእጅግ እድለ ቢሱ በስተቀር የማይገባባትን

16. ያ ያስተባበለና ከትዕዛዝም የሸሸ እድለ ቢስ (ነው የሚገባባት)።

17. አላህን በጣም ፈሪ የሆነ በእርግጥ ይርቃታል።

18. ያ (ከወንጀል) የሚጥራራ ሲሆን ገንዘቡን የሚለግስ፤

19. ለአንድም ሰው በእርሱ ዘንድ ተመላሽ የሚሆን ውለታ ሳይኖርበት።

20. ከሁሉ በላይ የሆነውን የጌታውን ፊት (ውዴታ) በመፈለግ ብቻ (ይህንን የሰራ) ሲቀር።

21. እርሱማ ወደ ፊት (በሚሰጠው) በእርግጥ ይደሰታል።

የቁርኣን ፍቺ ትርጉም፦ Amharic Translation - Africa Academy፣ እትም 1.0.3፤ ከQuranEnc.com ያለ ምንም ለውጥ የቀረበ። (QuranEnc.com)

ትርጉም የቁርኣንን ፍቺዎች ያስተላልፋል እንጂ ራሱ ቁርኣን አይደለም፤ ቁርኣን ከላይ ያለው የዐረብኛ ጽሑፍ ነው።

ቲላዋዎቹን አዳምጥይህን ሱራ በሙስሐፉ ከተፍሲር ጋር አንብብ‹ ሱራ አሽ ሸምስሱራ አድ ዱሓ ›